...

1 min read
-1

Some call it overthinking... ግን ምን ያክሎቻችሁ የድሮ ጓደኝነት ቅርርባችሁ ይናፍቃችኋል? በየራሳችን ዓለም ስንሮጥ ያጣናቸው/ የምናጣቸው ሰዎች እንዳሉስ አስበን እናውቃለን?

ብዙ የኔን ድንበር በር ታግዬ አንተ ጋር መምጣቴን በምን ቃል እንደማስረዳህ አላውቅም እንዲሁ ላወራ መጀመሬ ትልቁ ማስረጃዬ እንደሆነ ይሰማኛል ግን አንተ አይገባህም ጊዜህ ሚወሰድብህ ይመስልሀል ወይም ሳወራ አስደብርሀለው መሰለኝ አሁንማ አይንሽን ላፈር ካልከኝ ክረምት አልፎ በጋው ተገባደደ።

ሳወራህ ደስ ይለኛል አብሮ አደግ ጓደኛ አለኝ እያልኩ አፌን ሞልቼ እንዳወራ ይረዳኛል ከዛም በላይ ግን ጥንካሬዬ ነህ የእውነቴን ነው አሁን ያለንበትን ደረጃ አይቼ አይደለም ቁጭ አርገህ ባትመክረኝም ባንተ ተመክርያለው እንደቀልድ ባወራሀቸው ነገሮች ከስህተቴ ተምርያለው ድካሜን ሳልነግርህ መፍትሄ አግኝቼ በርትቻለው... አማክሬህም በህይወቴ ትልቁን ውሳኔ ባንተ እርዳታ ወስኛለው 

ግን ይሄን ሁሉ አንተ አታውቅም ስለነዚህ ነገር አላወራንማ

ሰዎች ወዳጅነትን አጠንክረው እንዴት እንደሚኖሩ ሳስብ ግራ ይገባኛል ምክንያቱም ልቀርብህ የተራመድኳት እያንዳንዷ እርምጃ አንተን ወደዛ በሁለት እርምጃ ያርቅብኛል ልቤ ማዶ ሩቅ ያለ ይመስለኛል ዘመን ዕድልና ጊዜ ብቻ ያራራቁን አይመስለኝም።

እኔ ምለው ሳላውቀው ማጠፋቸው ጥፋቶች ይኖሩ ይሆን?

ልትቀርበኝ ጀምረህ መልሰህ ስትርቀኝ ካንተ አለመፈለግ ጀርባ የኔ የጥፋት እጅ ይኖር ይሆን ብዬ ሰጋው..... እስቲ ንገረኝ መብከንከኔ ይለይልኝ እኔን አለመፈለግ ወይስ የኔ ጥፋት ከኔ ሚያርቅህ?

Comments (0)
No comments yet