INDELIBLE INKS

indelible-inks

"የተውኩትን ነገር ተመክሬ ተነግሬ ባገር ምን ጎትቶ አመጣብኝ? ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር?"

[እሷ]

ለሊት 7 ሰአት እንቅልፍ እንቢ ሲላት ፣ ለስላሳ ሙዚቃ በስሱ ከፈተች። ዘሪቱ እንደለመደችው ታለቃቅሳለች።

"ቀን ቀን ስራ አይጠፋም

አስሮ የሚያውለኝ

የማያስተክዘኝ

የማያሳስበኝ ....

ሲመሽ ግን አልችልም

ሰማዩ ሲጠቁር...."

  " እናሽን!" ሳታስበው ተነፈሰች።ዘሪቱ  እንባዋን ገፋፍታ የሽፋሽፍቷ ጫፍ አደረሰችው። ለራሷ ግን ውሸት መናገሩን አላቆመችም  ነበር። "I Still got this"  በንዴት next  በተኑን በጣቷ ረገጠችው።

ከስንት አመት በኋላማ  ደግሜ አላለቅስም ያውም በተረሳ ፣ በተተካ ወንድ ? ”

(Her conscience was asking tho... You really past him?)

ፕሌይሊስቷ በሙሉ ከዚህ በባሱ dark love ዘፈኖች እንዳልታጨቀ ባለማመን ይሁን ፣ ራሷን ለመፈተን በመፈለግ ጫፍ በወጣ የearphone volume ሙዚቃ ማዳመጡን ቀጠለች።

"በጎ ነኝ አልልም የባሰብኝን

ድኛለሁ አልልም የታመምኩትን

በናፍቆት ማንባቴ ፣እንቅልፍ ማጣቴን

በኔ ቦታ ሆኖ ማን አየው ጉዳቴን ...

ተረታሁ ..."

ሳግ አፈናት፣ እንባዋ ሊፈነቅል ታገላት። አመታት ያለፈው ፍቅር ምናባቱ ሊሰራ ዛሬ ትዝ አላት?  ቢያስረሳኝ ብላ የአሁን ወዳጇን ፎቶ በርብራ ታፈጥበት ገባች። ከቀድሟ ወዳጇ በላይ መልከኛ ነው።

"I have a cuter lover now... ምን ይፈጠር ነው ምትይኝ ሳሮን?"

ከራሷ ጋር መጨቃጨቅ ጀመረች።  እንባዋ ግን መገስገሱን አላቆመም። ይለይለት ብላ ፣ ማልቀሷ እውን እንዲሆን ዘፈን መርጣ ከፈተች።

"የተውኩትን ነገር ተመክሬ ተነግሬ ባገር

ምን ጎትቶ አመጣብኝ?ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር?"

ጉንጯን ኩልል የሚል እንባ አራሰው። በዝምታ እራሷን እስኪያማት ማልቀሷን አላባራችም። GiGi was her recipe for an all nighter crying party...የጂጂን የመጨረሻ አልበም ለመጀመሪያ ጊዜ ልብ ብላ እንድትሰማው የሰጣት እርሱ ነበር። GiGi ን ነፍሱ እስኪወጣ ይወዳታል ፤

"ከኔና ከጂጂ ማንን ይበልጥ  ትወዳለህ?" 

ብላው አኩርፏት ሁላ ነበር።   ነጋ።ምንም እንዳልተፈጠረ ፣ ወፍራም ቡናዋን በጠዋት ጠጥታ ወደ ስራዋ ሄደች። ስትስቅ ለሚያያት ፣ ለቅሶ ቤት ያደረች አትመስልም። ጥንካሬዋ ግልፅ ነበር።

* * * * * * ***

[እሱ]

"I'd spend 10,000 hours

and  10,000 more

Oh, if that's what it takes

to learn that sweat heart of yours"

ከንፈሩ ላይ ቀላል ፈገግታ ነበረች። this used to be his fav. Song ሳሮን  አጠገቡ እያለች።  ሳያስበው የመኪናውን ዳሽ ቦርድ መታው። እንዲህ ትጠላኛለች ብሎ አስቦ አያውቅም ።

"she has moved on. She's got a man,  ያውም ቆንጅዬ" አሰበ።

Last time he stalked her,  she was walking under the embrace of another man. And they kissed...So he's going for a date to replace her. ራዲዮው  ይዘፍናል።

" Here's to the ones that we got

Cheers to the wish you were here,

but you're not...

Cause the drinks bring back all the memories

Of everything we've been through...." 

Comments (3)
No comments yet