[ አውቃለሁ]

The things we don't say out loud but known to the heart
ቆንጆ ሴት ውብ እንስት አይደለሁ አውቃለሁ
አይኖቼም ጨረቃን አይመስሉም አውቃለሁ
ፀጉሬ ሀር እንዳይደል ይሄንን አውቃለሁ
ፈገግታየዬም ብርሃን እንዳይረጭ አውቃለሁ
ባትወደኛ ኖሮ ባጠገብህ ባልፍ
ዞረህ ቆም ብለህ አታይም አውቃለሁ
ለእናትህ ስትነግራት ፎቶዬን ስታሳያት
አመለ ሸጋ ናት ስነስርአት ያላት
ጨዋ ያሳደጋት
ብለው እንዳለፉ ባልሰማም አውቃለሁ
ለጓደኞችህም ሳታሰተዋውቀኝ
3ቱን ወር ትምህርቴን
3 ቱን ወር ፀባዬን
እግዜሩን መፍራቴን
ስትነግር እንደከረምክ ሳትነግረኝ አውቃለሁ
ሲያዩት ያላማረ ብለዉ እንዳይተፋኝ
በብዙ እንደደከምክ ይሄንን እረዳለሁ
ያገር ምድሩ ባለ ቅኔ ስለ ቆንጆ ሲቀኝ
ግጥም ሲደረድር ዜማውን ሲሰድር
ልትጋብዘኝ ወደህ ሁለቴ አስበህ
ስንኙን መርምርህ
እንደምትተወው
ባትልም አውቃለሁ
ግን አብረን ስንሆን
በጨዋታ መሀል
አለ አይደል አንዳንዴ
እኔን ደስ እንዲለኝ
ታምሪያሽ ግን በለኝ