መለያየት ሞት ነው!

1 min read
malayaayate-mote-nawe

ትንሽዬ ቁልፅል ግጥም።

መለያየት ሞት ነው

መለያየት ሞት ነው ለተነጣጠልነው፣

ሞት ሆኖ ሲሰማን በፍቅር ለኖርነው፣

ቀዬ መንደሩን ትተን ስደት ለመረጥነው።

መለያየት ሞት ነው...

በትዝታ ሄደህ በሃሣብ ብትመርሽ፣

ባለፈበት ጊዜ ተኝተህ ብታመሽ።

አንዴ ተለያይተህ ምንም አታመጣም፣

መመለስ ካልሆነ ሌላስ አያዋጣም።

ህይወት እርቆብህ ገደል ቢጨምርህ፣

ሽቅብ ለመንጠልጠል አቅሙ ቢያቅትህ፣

መለያየት እንኩዋ ሞት ሆኖ ቢሠማህ።

ሞቱን አሸንፈህ ድል ነስተህ ምትወጣው፣

ምናብ ህሊናህን መኖር ስትጀምር ነው።

ተመልሠህ ሄደህ ድሮህን ስታገኝ፣

ትናንትናን አቅፈህ ፣ ስመኸው ስትገኝ።

ጥቅምት,፳፻፩፪ዓ.ም

Comments (0)
No comments yet