ከትፍስህት ጋር

1 min read
katefesehete-gaare

አንድ በረንዳ ላይ ከብዙ ምሽቶች ውስጥ የንጋት አጥቢያው ላይ

ኡኡኡኡኡፍፍፍ ደከመኝ፣ መረረኝ

ምነው?

በቃ አልቻልኩም። እለፋለው እደክማለው ግን ሰባራ ሳንቲም ድንቡሎ አይከፈለኝም

አረ እንዴት?

በቃ ጠዋት ተነስቼ የግንባታ ስፍራው እደርሳለው። ሁሌም በመግቢያ ሰዓቴ ነው ምገኘው። ለራሴም ዛሬ ስራ እንደምንም እንደምሰራ ደሞዝም እንደሚከፈለኝ እነግረዋለው፣ ከትላንት ዛሬ እንደሚሻል አሳምነዋለው።

ከዛስ?

ከዛ. . . በቃ ሁሌ ደስተኛ ለመሆን እሞክራለው። አንቺም ታውቂያለሽ ሁሌ እንደሳቅሁ ነው። ዱዲ ባይኖረኝ እንኳን እንዲች ብዬ አላማርርም። እግዜሩ ረስቶኝ ይሆን? መቼም እስከናካቴው ትቶኝ ነው ሚሆነው። አየሽ ለእሱም ሰለቸሁት ማለት ነው።

ነው ብለክ ነው?

አዎ! እንዲያ ባይሆንማ እንዲ በትግዕስት እና በትልቅ ተስፋ እየጠበኩ ጥቂት እንኳ ደሞዝ አላጣም ነበር።

ስራው አድካሚ ነው?

እያወቅሽው በቃ ብርዱ ንፋሱ ከዛም ጸሀዪ ሲያሰቃየኝ ነው ምውለው። ማታ እንዴት እንደሚደክመኝ ባየሽ። ቲሽ ድካም ብቻ

እሱስ ይደክማል ግን ያንተ ስራ ምንድን ነው?

ማለት?

የስራ ድርሻህ ማለቴ ነው

እሱማ ያው ሲሚንቶ እና አሸዋ ማብኳት ነው። አካፋዬም ተደግፌው ቆሜ ሰለምውል ነው መሰለኝ ተጣሟል። አድካሚ ነው በጣም።

ቆሜ ስለምውል አልከኝ?

አዎ. . . ቆሞ መዋል አድካሚ ነው።

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

መውደድ መወደድን ናፍቀን ፍቅርን ላልተረዳን፣ ታመናል እያልን መዳንን ለጠላን፣ ከመድሀኒት ይልቅ ጠያቂ ለምንሻ፣ ከእውነታው ይልቅ ህልማችን ለጣመን፣ ዛፉን ሳንተክለው ጥላውን ለሻትን ለእኛ ሰርተን ሳይሆን ቆመን ለደከመን

Comments (0)
No comments yet