ኡኡኡ… ክፍል 3

uuu-kefele-3-4

Motherf**ker Vs እናትህ ት*ዳ

በክፍል ሁለት አማረኛ በግልጽ ለመነጋገር የምንፈልጋቸው ርዕሶች እንዲሰቀጥጡን እያደረገን እንደሆነና በሆነ መንገድ ለዚህ መፍትሔ መፈለግ እንዳለብን ገልጬ ነበር የተለያየነው። አንዳንዴ አማረኛ ግራ ይገባኛል። እንዴት ግራ እንደሚያጋበኝ በስድባችን ላስረዳችሁ። የሐበሻ ባለጌ ሲሳደብ እናትህ ት*ዳ ይላል። ፈረንጅ ደግሞ motherf**ker ይላል። የሐበሻው ስድብ የተሰዳቢው እናት ላይ ያነጣጠረ ነው። የፈረንጁ ግን በቀጥታ የተሰዳቢውን ብልግና እናትን የሚያህል ነገር እንኳን የሚደፍር በማለት ይገልጻል። እናት በጸነሰች፣ ባረገዘች፣ እህህህ ብላ በወለደች፣ ወገቧን አስራ ተሸክማ ባሳደገች፣ ጥርሷን ነክሳ ለቁም ነገር ላድርስ ባለች፣ እንደማንም ወጠጤ ትዘረጠጣለች። አንዳንዱ እንዲያውም አልፎ እናትህን ል*ዳ ይላል። ምንም የማታውቀው እናት ያውም በእንደሱ አይነት ባለጌ...

ከዚህ የተነሳ ለአስተዋይ ሰው መ*ዳት የሚለው የአማረኛ ቃል በጣም አስጸያፊ ነው። ቃሉን ከዚህ በፊት ሲጠቀሙት የሚያውቃቸውም ሰዎች ፈር የለቀቁ ባለጌዎች ናቸው። ስለዚህ እርሱ ይህን ቃል በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ለመጠቀም ቢያስብ እነዚያን ሰዎች የሆነ ስለሚመስለው ከአፉ ይመልሰዋል። ሌላኛው አማራጭ ወሲብ ነው። የወሲብ ግንኙነት…። የት ነው የማውቀው ይህን ቃል??? የኮንዶም ማስታወቂያ ላይ ነው መሰለኝ። መቼም ቢሆን አንድ ባል የሚስቱ ሰውነት ሲናፍቀው “ወሲብ እንፈጽም?” ብሎ እንደማይጠይቃት እርግጥ ነው። እንፈጽም የሚለው ቃል በራሱ ስሜትን ይገድላል። Let’s have sex ቢል ግን የሚከብድ ንግግር አይደለም። ፍትወት ነው ሌላው አማራጭ፣ ዝም ብዬ ልለፈው። ግብረ ስጋ ነው ደግሞ ሌላኛው፣ ቃሉ ራሱ አረፍተ ነገር በሉት። በዚህ ውስጥ ላሳያችሁ የፈለኩት እንዲህ አይነቱ ርዕስ ላይ በግልጽ ማውራት ምን ያህል ከባድ ነገር እንደሆነ ከቋንቋችን እንደምንረዳ ነው። ሁሉም ሰው በየጥጋ ጥጉ በአንድም በሌላም ተጎድቶበት ሊያወራው የሚፈልገው ጥብቅ ጉዳይ ሆኖ ሳለ ምናልባት እያፈረ ከጀሌዎቹ ጋር ካላወራው በስተቀር በቁም ነገር ከአዋቂ ጋር አይመካከርበትም።

ይኸ ችግር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቶ አሁን ፖርን የወጣቱ የመኝታ ቤት ምስጢር ሆነ። ማንም ሊነግረው ያልቻለውን ነገር እዚያ ላይ ሲያይ ምንም በማያውቀው አእምሮው ውስጥ የሚጋልበው ፈረስ ሆነ። Sex እያለ search ያደርግ የነበረው እየጋለበ፣ እየጋለ ወደ ተመረጡ porn sites፣ ወደ ተመረጡ ዘውጎች፣ ሴቶችን የፍትወት ማርኪያ እቃዎች አድርጎ ወደማሰብ፣ ወደ ስንፍና፣ ወደ አዝቅት… እየጋለበ!!!

ስለዚህ የሐበሻ አእምሮ በዚህ ሱስ ሲያዝ አንድ ውዥንብር ይፈጠርበታል። ይኸን ነገር ለምን አላወሩልኝም፣ እንደዚህ አይነት አስደሳች ነገር ለምን ተደበቀ የሚል እንዲሁም በተቃራኒው ይኸ ነገር ግን ትክክለኛ ነገር ነው? በገሃዱ አለም መፈጸም የሚችል ነው? የሚጠቅም ነው? የሚል። አንባቢዎች ምን ትላላችሁ?

Comments (0)
No comments yet