ኡኡኡ... ክፍል 2

uuu-kefele-2

የፖርን ሱስ ኡኡኡ ይልቀቀን!! ግን ፖርን ምንድነው?

የሆነ ልጅ ነኝ። ከዚህ ቀደም ''ኡኡኡ… '’ በሚል ርዕስ ባዘጋጀሁት ጽሁፍ በኢትዮጵያ የፖርን ተመልካቾች ቁጥር ምን ያህል እየበዛ እንዳለ አንስቼ ይህ አደጋ ስላለው መጋፈጥ እንዳለብን ጠቅሼ ነበር ያቆምኩት። ግን ለምን? ምንድነው ማካበድ? እንጃ። እስኪ እንመራመር…

በመጀመሪያ… ፖርን ምንድነው?

እንግዲህ የዚህ ዘመን ወጣት ሆኖ ፖርኖግራፊ ምን እንደሆነ የማያውቅ አለ ማለት ዘበት ነው። በእርግጥ በተወሰኑ ቃላት ፖርን እንዲህ እንዲህ ነው ብለህ ግለጽ ተብሎ ሰው ሁሉ ቢጠየቅ የየራሱ የተለያየ አተረጓጎም ሊኖረው ይችላል። ቢሆንም ግን የሰዎች የወሲብ ግንኙነት ላይ ትኩረት ያደረገና የተቀባዩን የፍትወት ስሜት መቀስቀስ የሚችል የስነ ጥበብ ስራ እንደሆነ ብዙሃኑ ይስማማበታል። በ inspirational public speaking እና counseling የሚታወቀው ኤርሚያስ ኪሮስ Daily Injera ላይ በሶስት ክፍሎች ባወጣው ''ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል!'' የተሰኘ Article ፖርኖግራፕፊን ''ማንኛውም የወሲብን ስሜት የሚቀሰቅሱ ወሲባዊ ታሪኮች፣ ፊልሞች፣ ፎቶግራፎች እንዲሁም የቃላት ልውውጥ'' በማለት ይገልጸዋል። አያይዞም ''ስለ ፖርኖግራፊ ጥናቶች ምን ይላሉ?'' ብሎ የሚከተሉትን ይዘረዝራል።

-ስለፖርኖግራፊ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለፖርኖግራፊ ተጋላጭ የሚሆኑት ከ11 ዓመታቸው ጀምሮ ነው።

-በኢንተርኔት ውስጥ ከሚገኘው ወደ ግማሽ የሚሆነው መረጃ ፖርኖግራፊ ወይም ከፖርኖግራፊ ጋር ተያያዥ የሆነ መረጃ ነው።

-በየቀኑ ኢንተርኔት ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 25% የሚሆኑት ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ናቸው።

-ከኢንተርኔት ላይ ከሚወርዱ ቪዲዮዎች መካከል 35% የሚሆነው ከፖርኖግራፊ ጋር የሚገናኙ ናቸው ።

-34% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሳይፈልጉት በማስታወቂያዎች በራሳቸው ብቅ በሚሉ ሌሎች መረጃዎች ምክንያት ለፖርኖግራፊ ይጋለጣሉ።

-አለም ላይ ካሉ ድህረ ገጾች መካከል 12% የሚሆነው የፖርኖግራፊ ገጾች ነው።

-በአለማችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች መካከል፣ በፖርኖግራፊ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይገኙበታል።

-በሰሜን ኮሪያ በሐገሪቱ ውስጥ ፖርኖግራፊ ነክ የሆኑ ነገሮችን ማሰራጨትም ሆነ ማየት በሞት የሚያስቀጣ ነው።

ከእነዚህ መረጃዎች የምንረዳው በዚህ ዘመን ፖርኖግራፊ ምን ያክል በብዙሃኑ እጅ በቀላሉ መግባት እንደቻለ ነው። ነጮቹ ይህን ክስተት Pornification of Society ይሉታል።

የ11 ዓመት ህጻን ማለት እንግዲህ ልጅ በየት በኩል ከእናቱ ሆድ እንደሚወጣ ሲያስበው ግራ የሚገባውና ሁሌ እናቱን የሚጠይቅ ነው። ገና በዛ እድሜው ሴት ልጅ ጸጉራ ተጨምድዶ ተይዞና በአፏ ዘነዘና የሚያክል የሆነ ነገሩን አንዱ ከቶባት ሲወዘውዛት ማየት ምን አይነት የተበላሸ አመለካከት እንደሚፈጥር ለመገመት አያዳግትም። ገና ምንም ባልተጻፈበት የብላቴና አእምሮ ጭከና በተሞላበት ሁኔታ ሴቶች ሲንገላቱ፣ በዛም ወንዱ ሲደሰት መመልከት ምቼም የማይረሳ ጠባሳ ፈጥሮ ያልፋል። የሚያሳዝነው ደግሞ ልጆች ምንም እንኳን የሚያዩት ነገር ልክ እንዳልሆነ ቢጠረጥሩም ሰውነታቸው ግን ከዚያ በፊት ተሰምቶት የማያውቀው ልዩ ስሜት ሲሰማው ይታወቃቸዋል። ያም ስሜት አድጎ አድጎ ምን አይነት ከፍታ ላይ እንደሚደርስ ለማወቅ ይጓጓሉ። Vaseline ስለሚሰጠው ልዩ ጥቅም የሚሰሙትም በዚሁ ወቅት ነው።

እዚህ ላይ የደረሰ ልጅ ከዚያ በኋላ ስራው እያሳደደ እዛ ከፍታ ላይ ሊያደርሱት የሚችሉ ነገሮችን መፈለግ ይሆናል። በእዚህ ወቅት የሚደረጉ ነገሮች በጤናማ የሰው አእምሮ ይሆናሉ ተብለው የማይገመቱ ናቸው። እያንዳንዱ ልጅ ራሱን ለማርካት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ያችን ለማግኘት ይንቆራጠጣል። ባልጠበቀው ሰዓት ስሜቷ ትዝ ትለውና የሚያደርገውን ታሳጣዋለች። በሆነ መንገድ ብቻ የተወጣጠረው ነገሩን ማስተንፈስ ይፈልጋል። ሽቅብ ይወጣል... ቁልቁል ይወርዳል... ይተነፍሳል... ያምጣል… ይመኛል... አይኑን ይጨፍናል… ይጨርሳል። መጦ ያወጣውን የሚያረግበት ይፈልጋል... ማንም እንዳላየው ያረጋግጣል... ያኔ… የሚጠላው ህሊናው ብቅ ይላል። የጸጸት አዘቅት ውስጥ ይገባል። በሳቅ በጨዋታ ሲቦርቅ የሚፍለቀለቅ ፊቱ አንዳች ጥላ ያጠላበታል። የጥላቻን ምንነት በቅጡ የማያውቅ ልቡ ራሱን መጸየፍ ይጀምራል።

ችግሩ የሚጀምረው አእምሮ ውስጥ እንጂ መራቢያ አካል ላይ አይደለም። መራቢያ አካል የሚለውን ስጽፍ አማረኛው ሰቀጠጠኝ። እንግሊዝኛ በዚህ በዚህ እኮ አቤት ሲመችችች። D**k እኮ ኖርማል ነው። መራቢያ አካል… ኣኣኣክ ቱ። በቀጣይ ስመጣ በቃ ጥሩ ቃል ፈልጌለት እመጣና እሱን እንጠቀማለን። ይህን ጽሑፍ ለምትወዷቸው እንደቀልድ አድርጋችሁ አካፍሏቸው... ምናልባት ከትልቅ ቀንበር የሚገላገሉበት ይሆናል። እስክ ቀጣዩ... በቸር ቆዩ...

Comments (0)
No comments yet