መፀሀፈ-ፊስአልጎስ

1 min read
matzahafa-fisealegose

የጥንት አባቶቻችን ጥበብ እና ብልሀት እጅግ ያስገርማል።በተለይም በቀላሉ የምናየው አስተውሎት በህይወታችን ምን ያክል ተፅዕኖ እንዳለው ተገንዝቤበታለው። በዙሪያችን የምናየው እና የምንሰማው በኛ ቁጥጥር ስር ነው?

".....ስለዚህ ነገር ሰለሞን ተራቀቀና በአየር ውስጥ የሚበር ታላቅ ንስርን ያዘ፤በቤት ውስጥም በማሰሪያ አሰረው፤ነጭ ሴት ፈረስንም አመጣ።ለብቻው ከንስር በቀር ወዲያ እና ወዲህ ሌላ ነገር እንዳትመለከት ለአይኖቿ መጋረጃን አደረገ፤ንስሩ ብቻ ወዳለበት እንጂ ወደኋላ እና ወደሌላ እንዳትመለከት አደረገ።ከዚህ በኋላ በኋላዋ በኩል ወንድ ፈረስን አቀረበ ያን ግዜም ያቺ ፈረስ ፀንሳ በአየር ውስጥ እንደሚበረው እንደ ንስሩ ክንፎች ያሉት ወንድ ፈረስን ወለደች።አፉም እንደ ንስር ሲሆን ሁለቱ ጆሮዎቹ እና እግሮቹ እንደ ፈረስ ነው......." 

በጣም ያስገረመኝ መፀሀፍ ነው። ያለ ምንም #ጀነቲካል ኢንተራክሽን በማየት ብቻ የተለየ ፍጥረትን መፍጠር መቻል የሚገርም ነገር ነው። በፅንሰት ግዜ የምናየው ነገር በሚወለደው ልጅ ላይ ትልቅ መገለጥ እንዳለው በተለያየ ምሳሌ ያሳወቀኝ መፀሀፍ ነው። 

በህይወታችን ደጋግመን ያየነው እና ደጋግመን ያሰብነው ነገር ፅሎታችን እሱው ነው። ምን ላይ ነው አተኩረን ያለነው? ስለ አእምራችን አሰራር ትንሽ ማውቅ ብንችል ትልልቅ ነገሮችን በህይወታችን መፍጠር እንደምንችል ይሰማኛል። 

#አንቅህ_ዲጂታል_መፅሄት

#መፀሀፈ_ፊስአልጎስ

#መጋቤ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

Comments (0)
No comments yet