ባለድርሻ

baaladereshaa

ድባቴ (መደበር) ምንድን ነው? ምን ምን መገለጫዎች አሉት

  • ከፍተኛ የሆነ ሀዘን፤ ማልቀስ፤ ባዶነት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲስተዋል።
  • ንዴትን መቆጣጠር አለመቻል፤አብዝቶ ዝም ማለት(ብቸኝነትን መምረጥ)፤ አለመረጋጋት ወይም ምንጩ ያልታወቀ የፍርሀት ስሜት መኖር።
  • የመደበኛ የህይወት እንቅስቃሴዎች ላይ ስሜት ወይም እርካታ አለመኖር።
  • የእንቅልፍ ችግር (እንቅልፍ ማጣት ወይም አብዝቶ መተኛት )።
  •  ምንም ዓይነት ተግባርን ሳይከውኑ አልያም በትንንሽ ተግባራት የመድከም እና አቅምን የማጣት ስሜት።
  • ቀሰስተኛ የሆነ ንግግርን ማድረግ፤ በአንድ ሀሳብ ላይ አለመርጋት ወይም ለማሰብ መቸገር።
  • ዋጋ የለኝም ብሎ ማሰብ፤ ምክንያቱ በግልፅ ያልታወቀ የፀፀት ስሜት እና ባለፈ ታሪክ እና ትውስታ መጨነቅ/ማብሰልሰል።
  • የአካል ክብደት መለወጥ ( ውፍረት መጨመር ወይም መቀነስ)።
  • ከፍተኛ የሆነ ራስን የማጥፋት ሀሳብ እና ሙከራዎችን ማድረግ።
Comments (0)
No comments yet